የHUAWEI ኤአር መለኪያ እና ግላዊነት መግለጫ
በመጨረሻ የተዘመነው፦ ሴፕተምበር 26፣ 2022
የHUAWEI ኤአር መለኪያ የገሃዱን ዓለም ነገሮች እና የሰው አካላትን ለመለካት የሚያስችልዎ በ Huawei Device Co., Ltd. (ከአሁን በኋላ "Huawei"፣ "እኛ"፣ "በእኛ" ወይም "የእኛ" በመባል የሚጠራ) የቀረበ መተግበሪያ ነው። Huawei የግል መረጃዎን እና ግላዊነትዎን አክብዶ ነው የሚያየው፣ እና በሚመለከታቸው ህጎች እና በጸኑ የኢንዱስትሪ ደህንነት መስፈርቶች መሠረት የግል መረጃዎን ለመጠበቅ አግባብ የሆኑ የደህንነት እርምጃዎችን ለመውሰድ ቆርጦ የተነሳ ነው።
1 የእርስዎን የግል መረጃ እንዴት ነው የምንሰበስበው እና የምንጠቀምበት
በ የHUAWEI ኤአር መለኪያ በኩል ከታች የተገለጹትን ባህሪያት ለእርስዎ እናቀርባለን። የውል ግዴታዎቻችን ለማሟላት እና እንደዚህ ያሉ ባህሪያትን መጠቀም መቻልዎን ለማረጋገጥ፣ ሲጠቀሙባቸው ከታች እንደተገለጸው እንደዚህ ያሉ ባህሪያትን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን መረጃ እናሰናዳለን። ተዛማጁን መረጃ የማያቀርቡ ከሆነ በዚህ መተግበሪያ ውስጥ የእርስዎ የባህሪያት አጠቃቀም ተጽዕኖ ያድርበታል።
ነገሮች እና ሰዎች መለካት
የአንድን ነገር ርዝመት፣ ስፋት እና ይዘት ለመለካት እንዲሁም የሰዎችን ቁመት፣ የልብ ምት እና የትንፈሳ ፍጥነት (የባህሪ መገኘት እንደ መሳሪያ ሞዴል ሊለያይ ይችላል) የእርስዎን የካሜራ ቅድመ እይታ ዥረት፣ የአክስለሮሜትር መረጃ፣ የጋይሮስኮፕ መረጃን፣የመሬት ስበት ዳሳሽ መረጃ፣ የማግኔቶሜትር መረጃ፣ የማያ ቅኝት ዳሳሽ መረጃ፣ የስርዓት ንብረቶች እና የመሳሪያ ሞዴል በአገር ውስጥ ማካሄድ አለብን። የመለኪያዎችን ስክሪንሾቶች ለማንሳት እና ለማስቀመጥ ኤአር መለኪያን ከተጠቀሙ፣ የእርስዎን ስክሪንሾቶች በመሳሪያ ላይ እናሰናዳ እና እናከማቻለን።
በተጨማሪም የHUAWEI ኤአር መለኪያ የእርስዎን የነገር መለኪያ ውሂብ (ርዝመት፣ ስፋት እና ይዘት ጨምሮ) ከሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ጋር እንዲያጋሩ ይፈቅድልዎታል። ውሂቡ ከግለሰቦች ጋር አይገናኝም። የHUAWEI ኤአር መለኪያ ከሶስተኛ ወገን ሶፍትዌር ከማስጀመርዎ በፊት፣ እባክዎ የሶስተኛ ወገንን የግላዊነት ፖሊሲውን በጥንቃቄ ያንብቡ።
2 የሚያስፈለጉ ፈቃዶች
ካሜራ፦ የዚህን መተግበሪያ የመለኪያ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ በካሜራ ቅድመ እይታ ዥረት የኤአር ስልተ ቀመሮችን በመጠቀም የገሃዱን ዓለም ነገሮች እና የሰው አካላትን ለመለየት ይህ ፈቃድ ያስፈልገናል። ይህን ፈቃድ ካልሰጡ፣ የዚህን መተግበሪያ የመለኪያ ባህሪ መጠቀም አይችሉም።
ማከማቻ (ወይም ሚዲያ እና ፋይሎች)፦ የመለኪያ ውጤቱን ለማስቀመጥ አዝራሩን ሲነኩ የመለኪያዎችን ስክሪንሾቶች እንድናነሳ እና እንድናስቀምጥ ይህ ፈቃድ ያስፈልጋል። እንዲህ ያሉ አገልግሎቶች የማያስፈልግዎት ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ይህን ፈቃድ መሻር ይችላሉ። በሌሎች አገልግሎቶች አጠቃቀምዎ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም።
በስርዓት ቅንብሮች በኩል የዚህ መተግበሪያ ፈቃዶችን ማስተዳደር ይችላሉ።
3 እኛን ማነጋገር
ለግል መረጃ ጥበቃ የተመደበ ልዩ ክፍል እና ሰራተኞች አለን። የግላዊነት ጥያቄዎች ገጹን በመጎብኘት ሊያነጋግሩን ይችላሉ። በተቻለን ፍጥነት ምላሽ እንሰጣለን።
በተቀበሉት ምላሽ ካልተደሰቱ፣ በተለይ የግል መረጃዎ አሰነዳዳችን ወይም አያያዛችን ህጋዊ መብቶችዎን እና/ወይም ጥቅሞችዎን እንደጣሰ ከተሰማዎት፣ በሚመለከተው የግዛት ህግ ስልጣን ውስጥ ባለው የሕዝብ ፍርድ ቤት በመክሰስም ሆነ በሚመለከታቸው የኢንዱስትሪ ማህበር ወይም የመንግስት ተቆጣጣሪ ወኪሎች ጋር ቅሬታ በማስገባት ወይም በሌሎች መንገዶች ውጫዊ መፍትሔ መፈለግ ይችላሉ። እንዲሁም ቅሬታዎን ለማሰማት ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን መስመሮች በተመለከተ እኛን ማማከር ይችላሉ።
የ Huawei የግል መረጃዎን መሰብሰብ እና መጠቀም በግላዊነት ፖሊሲያችን የሚተዳደር ነው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የHuawei ሸማች ንግድ ግላዊነት መግለጫ ይመልከቱ።